በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ባለማምጣታችሁ ምክንያት የማካካሻ ትምህርት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንድትወስዱ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም፣ የአቀባበልና የጋራ መግለጫ የሚሰጠው ሰኞ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 7 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም ይሆናል፡፡

ስለሆነም ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-

* የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* የፓስፖርት መጠን (Passport Size) የሆኑ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፎች እና
* አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ

በመያዝ ሁሉም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች  በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የስም ዝርዝራችሁ ከፊደል ተራ A እስከ S የሚጀምሩ በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው በጫሞ ካምፓስ እና የስም ዝርዝራችሁ ከፊደል ተራ T እስከ Z የሚጀምሩ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው በሳውላ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ ያሳውቃል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት