አቶ ዝናቡ ብርሃኑ ከአባታቸው አቶ ብርሃኑ አሰፋ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ሙቀነ ሙለቶ በቀድሞው ጋሞ ጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ ቦርዳ ቀበሌ ጥር 22/1988 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቦርዳ ሙሉ 1 ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሳውላ 2ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን ሀምሌ 30/2012 ዓ/ም ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአካውንቲንግ በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡

አቶ ዝናቡ ከነሀሴ 25/2009 ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በዩኒቨርሲቲው ሳውላ ካምፓስ ጠቅላላ አገልግሎት ዳ/ጽ/ቤት የጽዳት ሠራተኛ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ ዝናቡ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መጋቢት 25/2016 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አቶ ዝናቡ ባለትዳር እና የ5 ልጆች (3 ወንድ እና 2 ሴት) አባት ነበሩ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በአቶ ዝናቡ ብርሃኑ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት