መጋቢት 29/2007 ዓ/ም የመሠረት ድንጋይ የተጣለለት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፊታችን ሰኔ 01/2016 ዓ/ም ተመርቆ ወደ አገልግሎት ሊገባ ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡

ሆስፒታሉ 600 የሕሙማን አልጋዎችን እና የተለያዩ ዘመናዊ የመመርመሪያና የሕክምና ቁሳቁሶችን የሚይዝ ሲሆን ከፍ ያሉ ሕክምናዎችን ለማግኘት ወደተለያዩ ከተሞች የሚደረጉ ጉዞዎችን፣ ተጨማሪ ወጪዎችንና እንግልትን በማስቀረት ረገድ ከሰባት ሚሊየን በላይ በሚሆኑ የአርባ ምንጭና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተስፋ የተጣለበት ነው፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት