የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ የ2015/16 የሥራ ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ ለ2017/18 ለሁለት ዓመት የሚያገለግሉ አዲስ ሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ከግንቦት 3/2016 ዓ/ም ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ ምርጫ በየሁለት ዓመት የሚካሄድ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ የቆዩ፣ አማካይ ውጤታቸው 2.75 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣ በዲሲፕሊን ጥሰት ያልተከሰሱ እንዲሁም በሃይማኖት፣ በብሔርና በቋንቋ ልዩነት የማይፈጥሩና አብሮነትን የሚደግፉ ተማሪዎች በምርጫው መሳተፍ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
በዚህም መሠረት በመጀመሪያ ከሴክሽን አንድ ሴትና አንድ ወንድ ተማሪ የተመረጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ከአዲስ ፓርላማ አባላት ሦስት፣ ከቀድሞ አባላት ሦስትና በሴት ኮታ ያለምርጫ አንድ ሴት አጠቃላይ ሰባት አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡

በቀጣይ አስመራጭ ኮሚቴዎች የራሳቸውን የጊዜ ሰሌዳ በማዘጋጀት፣ መመልመያ መስፈርት በማውጣትና በየካምፓሱ ማስታወቂያ አውጥተው በመመዝገብ ለሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ብቁ የሆኑትንና ፍላጎት ያላቸውን በመለየት ለጠቅላላው ፓርላማ አቅርበው ምርጫ ይካሄዳል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት