የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ማዕከል በ2008 የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲው ለተመደቡ ከ5700 በላይ አዲስ ተማሪዎች ከመስከረም 24-25/2008 ዓ/ም በዋናው ግቢ አቀባበል አድርጓል፡፡ Click here to see the Pictures.

የተማሪዎች አገልግሎት ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ጳውሎስ ታደሰ እንደገለፁት ማዕከሉ በ2008 ዓ/ም በአንደኛ ሩብ ዓመት ክፍሉ ለማከናወን ካቀዳቸው በርካታ ተግባራት መከካከል ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች አቀባበል ማድረግ እና ዩኒቨርሲቲው ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በመሆኑም የዩኒቨርሲቲውን ፀጥታና ደህንነት፣ የትራንስፖርትና ስምሪት ክፍል፣ የተማሪዎች ህብረትና የሰላም ፎረም እንዲሁም የሌሎች ክበባት አባላትን በማስተባበር ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው ትራንፖርት ተማሪዎችን ወደ ተመደቡበት ካምሶች ያለ እንግልት እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡

በማዕከሉ የተማሪዎች አደረጃጀት ባለሙያ አቶ ሞላ ሞሊሶ በበኩላቸው ለሥራው ስኬት በየደረጃው ያሉ የተማሪዎች አደረጃጀቶችን በማቀናጀት እና ፈቃደኛ የሆኑ ነባር ተማሪዎችን በመመልመል 124 ወንድ ፣44 ሴት በድምሩ 168 ተማሪዎች መሳተፋቸውን ተናግረዋል፡፡

ተማሪ እመቤት መንገሻ በአቀባበሉ ደስተኛ እንደሆነች በተለይም ተማሪዎችን ያመጣው መኪና ዩኒቨርሲቲው ዋና ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲያወርድ መደረጉ ይደርስ የነበረውን እንግልት ማስወገዱን ገልፃ በቀጣይ የትምህርት ዘመን ለሚገቡ ተማሪዎች ተመሳሳይ አገልግሎት ለመስጠት እንድነሳሳ አድርጎኛልም ብላለች፡፡