በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በጎ አድራጎት ክበብ አባላት ከጥቅምት 22 እና 23/2011 ዓ/ም ጫማ የመጥረግ ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል፡፡
የክበቡ አስተባባሪ ተማሪ ዮሴፍ ድረሴ እንደገለፀው የጫማ መጥረግ ሥነ-ስርዓቱ መሠረታዊ ዓላማ የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው የኮሌጁ ተማሪዎች፣በአካባቢውለሚገኙ ጧሪ አልባ ለሆኑ አረጋውያን እንዲሁም ወላጅ አጥ ህፃናት የሚያግዝ ገንዘብ የማሰባስብ ሥራ ለመሥራት መሆኑን ገልፆ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የጫማ ጠረጋ ፕሮግራም ብቻ ከ3‚500 ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መቻሉን አስተባባሪው ተናግሯል፡፡ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ በ2008 ዓ/ም በ7 የህክምና ተማሪዎች የተመሠረተው ክበቡ አሁን ላይ ከ40 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን በ2010 በጀት ዓመት በሁለት ዙር የድጋፍ ፕሮግራም ለ2 የኮሌጁ ተማሪዎች፣ ለ70 ጧሪ አልባ አረጋውያንና ወላጅ አጥ ህፃናት የገንዘብ፣ የአልባሳት እንዲሁም ሌሎች ድጋፎችን ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን በ2011 የትምህርት ዘመንም ክበቡ የጀመራቸውን የበጎ አድራጎት ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡