የግርጫ ደጋ ፍራፍሬና አትክልት ምርምር ማዕከል የመስክ ጉብኝት ጥቅምት 12/2009 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ የጉብኝቱ ዓላማ በዩኒቨርሲቲው እየተሠሩ የሚገኙ ምርምሮች በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲተዋወቁ ማድረግና እየተጠናቀቀ የሚገኘውን የምርምር ማዕከል ግንባታ ምልከታ ማድረግ ነው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በኮንሶ ካልድሜ ንዑስ ቀበሌ ያሠራውን የውሃ ማሸጋገሪያ ድልድይ ሐምሌ 23/2008 ዓ.ም ለአካባቢው ማህበረሰብ አስረክቧል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2009 የትምህርት ዘመን 6125 አዲስ ተማሪዎችን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለማስተማር ተቀብሏል፡፡ የቅበላ መጠኑ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር ብልጫ ያለው ሲሆን ከአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ 2634ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ከስፖርት አካዳሚ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት መካከል በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በነጭ ሳርና አባያ ካምፓሶች የተሠሩት ደረጃቸውን የጠበቁ ጂምናዚየሞች፣ የእግር ኳስ ሜዳዎችና ኦሎምፒክ ስታንዳርድ የዉሃ ዋና ገንዳ ለግቢውና ለአካባቢው ስፖርት አፍቃሪ ማህበረሰብ ትልቅ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛሉ፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

Arba Minch University, one of the first generation universities in the country, poised to script a history, has taken a landmark decision to create fully autonomous ‘Water Technology Institute’ bifurcating the present Institute of Technology tentatively by January, 2017.