Arba Minch Institute of Technology (AMiT) in Arba Minch University in collaboration with DAAD Information Center in Ethiopia held a presentation program on free scholarship opportunities in Germany.Click here to see more photos.

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዓባያ ካምፓስ የ2016 ዓ/ም 1ኛ ዓመት ሴት ተማሪዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ አቀባበልና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ነባር ሴት ተማሪዎች የሽልማት አሰጣጥ መርሃ ግብር ጥር 08/2016 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡
ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ረ/ፕ ታደሰ አብርሃም ከአባታቸው ከአቶ አብርሃም ወርቁ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዘውዴ ተሰማ በቀድሞው ወሎ ክፍለ ሀገር በደሴ ዙሪያ ወረዳ መስከረም 3/1953 ዓ.ም ተወለዱ፡፡  ረ/ፕ ታደሰ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅግጅጋ እና በአፊሲን እንዲሁም የመለስተኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጋምቤላ፣ ጐሬና ባዕደማርያም ላቦራቶሪ ት/ቤቶች ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት ጋር በመተባበር “አርባ ምንጭ ታንብብ!” በሚል መሪ ቃል ታላቅ የንባብ ሳምንት አዘጋጅቷል፡፡ የንባብ ሳምንቱ በአርባ ምንጭ ከተማ ከጥር 18-21/2016 ዓ/ም ማለትም ከፊታችን ዓርብ እስከ ማክሰኞ ድረስ ድግሱ ለአራት ቀናት ይቆያል፤ ድንቅ መርሃ ግብሮች ተካተውበታል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የዩኒቨርሲቲው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሠላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆን ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

 መልካም በዓል!!