የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኔዘርላንድ ሀገር ከሚገኝ “KNCV Tuberculosis Foundation” ከተሰኘ ዓለም አቀፍ ተቋም ጋር በምርምርና መማር ማስተማር ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ጥር 7/2016 ዓ/ም ተፈራርሟል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የኢትዮጵያ ሥራና ክሂሎት ሚኒስቴር በየዓመቱ ብሩህ ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል  የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ያካሂዳል፡፡ በዚህ ውድድር አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ በማሸነፍ ከግንባር ቀደም ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ ይሰለፋል፡፡ በተመሳሳይ በ2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የብሩህ ኢትዮጵያ  የቢዝነስ ሃሳብ ውድደር ተማሪዎችን የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ሥልጠና በማሰልጠንና በማወዳደር የተሻለ ሃሳብ ያላቸውን ተማሪዎች ለብሩህ ኢትዮጵያ ወደ አዲስ አበባ የምንልክ መሆኑን እየገለፅን በዚህ ውድድርና ሥልጠና የነቃ ተሳትፎ እንድታደርጉ በአንክሮ እናሳስባለን፡፡ ምዝገባው የሚካሄደው  ከጥር 10 - 17/2016 ዓ.ም ሲሆን የቢዝነስ ሃሳብ ተወዳዳሪዎች በግል ወይም በቡድን መወዳደር ይችላሉ፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቀድሞው የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ባደረገው የማዕድን አለኝታ ጥናት በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ከ950 ሚሊየን ቶን በላይ የብረት እንዲሁም 429 ሚሊየን ቶን የድንጋይ ከሰል ማዕድን ከምችት መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ "Jhpiego" ጃፓይጎ ከተሰኘ መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በኮሌጁ በ“e-learning” የአካዳሚክ ሥራዎችን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር በሚያስችል የኦንላይን መተግበሪያ ፕላትፎርም አጠቃቀምና አተገባበር ላይ ልምድ ለማካፈል የተዘጋጀ የአንድ ቀን ወርክሾፕ ጥር 3/2016 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡