የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት በሥሩ ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና የሥራ ክፍሎች ጋር የ2018 ዓ/ም የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ፊርማ ሥነ ሥርዓት እንዲሁም የ2018 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ሪፖርትን በተመለከተ ከምርምር ካውንስል አባላት ጋር ጥቅምት 27/2018 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
በመርሐ ግብሩ የ2018 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም፣ የ2018 ዓ/ም የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI)፣ ጭብጥ ተኮር የምርምር ሂደቶችን የሚመራ ኮሚቴ መመሥረት፣ አዲስ የምርምርና ኅትመት መመሪያ፣ ‹‹Research and Outreach Management system (ROMS)›› የደረሰበት ሁኔታ በስፋት ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ እንደገለጹት እንደ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት ዓመት በመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ሥራዎች ላይ በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከስምንቱ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ውድድር ውስጥ እንደመሆኑ የሚመዘገቡ ስኬቶችና ውጤቶች የዩኒቨርሲቲውን አፈጻጸም ከፍ የሚያደርጉ ናቸው ያሉት ም/ፕሬዝደንቱ ሁሉም የሥራ ክፍሎች የገቡትን የሥራ ውል ለመፈጸም ተግተው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በውሉ መሠረት የሚፈጸሙ ተግባራት በአግባቡ መቀምጥ እንዳለባቸውና ካለፈዉ ዓመት ልምድ በመነሣት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በጋራ መሥራት እንደሚስፈልግም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በትምህርት ሚኒስቴር ከተቀመጡ ስምንት የማሻሻያ አጀንዳዎች ውስጥ አንዱ የምርምር ሥራዎች ማሻሻያ ሲሆን ከጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ጀምሮ ያሉ የምርምር ጭብጦች እየተከለሱ መሆኑን ም/ፕሬዝደንቱ ጠቁመዋል፡፡
የምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ሀ/ማርያም በበኩላቸው በዓመቱ ውስት ሦስት ጊዜ ከምርምር ካውንስል አባላት ጋር ምርምርን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ውይይት እንደሚደረግ ተናግረው በአሁኑ ውይይት ስድስት አጀንዳዎች ቀርበው ውሳኔ የተሰጠባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከቀረቡ አጀንዳዎች ውስጥ አንዱ አዲስ የምርምርና የኅትመት መመሪያ መውጣቱ ሲሆን እንደ አጠቃላይ በምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ሥር የሚሠሩ ሥራዎች ሂደት መገምገሙን፣ ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መሰጠቱን እንዲሁም የምርምር ሥራዎች ሂደትና አፈጻጸም ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

