የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ክፍል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከሦስት መቶ በላይ ለሚሆኑ ኢ-መደበኛ ተማሪዎች በ"e-SHE " ፕሮግራም ላይ ጥቅምት 29/2018 ዓ/ም በጫሞ ካምፓስ ኦረንቴሽን ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሮኒክ ት/ክፍል አስተዳደር ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ አበበ (e-SHE) በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተቀረጸና አሁን ላይ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እየተተገበረ የሚገኝ የኤሌክትሮኒክ አስተዳደር መሆኑንና ቀድሞ የነበረውን የትምህርት አሰጣጥ በመቀየር የኦንላይን ትምህርት ተደራሽ ማድረግን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ ዶ/ር መሐመድ ፕሮግራሙ ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው ትምህርታቸውን መከታተል የሚያስችልና "Student Success Suit(SSS)" ተማሪዎቹ የኦንላይን ትምህርት ከመጀመራቸው አስቀድመው ሊያውቁት የሚገባ ሥልጠና መሆኑን አስገንዝበዋል።
የተከታታይና ርቀት ትምህርት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ዶ/ር በለጠ ይልማ በበኩላቸው ዲጂታል ትምህርት የኢትዮጵያ አንዱ መገለጫ እየሆነ መምጣቱንና በሀገርና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ የሚገኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ለመምህራንና ለመደበኛ ተማሪዎች በዲጂታል ክሂሎት ላይ ያተኮሩ ሥልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ያወሱት ዶ/ር በለጠ የዩኒቨርሲቲው ኢ-መደበኛ ተማሪዎችም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማለም መርሐ ግብሩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ም/ዲን አቶ ፌኔት ሚዴቅሳ "e-Learning" የትምህርት ሥርዓት መዘርጋት አንዱ የሪፎርም አጀንዳ መሆኑና የተማሪዎቹን የጂታል ዕውቀት ለማሻሻል እና ዘርፈ ብዙ መረጃ ወደ አንድ ቋት ለማምጣት በኮሌጅ ደረጃ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

