8ው ዙር የማኅበረሰብ ጉድኝት ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ጥር 6/2016 ዓ/ም ተከብሮ ውሏል፡፡ በዕለቱም ዩኒቨርሲቲው በአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው የሚገኙ የተፈጥሮና የቱሪስት መስህብ ጸጋዎችን የሚያንጸባርቅ፣ ለከተማው ውበት ከፍ ያለ አበርክቶ ያለውና በ17.2 ሚሊየን ብር በከተማው መግቢያ ላይ ያስገነባውን አደባባይ ያስመረቀ ሲሆን የከተማው ማዘጋጃ ቤትና ማኅበረሰቡ አደባባዩ በጥንቃቄ እንዲያዝ በጋራ እንዲሠሩ ማሳሳቢያ ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የእናቶችንና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል በሚተገበረው ‹‹AMU-IUC›› ፕሮጀክት III ሥር ከሚከናወኑ ምርምሮች አንዱ የሆነውንና በጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ በነፍሰጡር እናቶችና ሕፃናት ጤና ሁኔታ ላይ በቪዲዮ የተመሠረተ የጤና ትምህርት የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለማወቅ የተደረገውን የሙከራ ጥናት ውጤት ለማኅበረሰቡ ለማስተዋወቅ ጥር 04/2016 ዓ/ም በጊዶሌ ከተማ ወርክሾፕ ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በግል የማካካሻ ትምህርት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 6/2016 ዓ.ም፣ የትምህርት ክፍያ የምትከፍሉት ከጥር 6 - 7/2015 ዓ.ም እና ትምህርት የሚጀመረው ጥር 8/2016 ዓ.ም ስለሆነ በግል ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ትምህርት እንድትጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡

እንግሊዝ ሀገር የሚገኘው የ''McGee Group'' ባልደረባ የሆኑት አቶ ሌም ብርሃኑ እና ሚስ ቤላ ቨርመንት/Ms Bella Vermunt/ በራሳቸው ተነሳሽነት ያሰባሰቧቸውንና ለአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የሚያገለግሉ 100 የምኅንድስና ሳይንስ ዘርፍ መጽሐፎችን በስጦታ አበርክተዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ባለማምጣታችሁ ምክንያት የማካካሻ ትምህርት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንድትወስዱ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም፣ የአቀባበልና የጋራ መግለጫ የሚሰጠው ሰኞ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 7 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም ይሆናል፡፡