- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ከ2,500 በላይ የቅድመና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ሰኔ 26/2016 ዓ.ም በጎፋ ሳውላ ከተማ ሳውላ ካምፓስ እና ሰኔ 27/2016 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ አባያ ካምፓስ ያስመርቃል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 36 ዙር ምረቃዎች ከ82,000 በላይ ብቃት ያላቸው ምሩቃንን በማፍራት ለሀገራችን ልማትና እድገት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ያለ አንጋፋ ተቋም ነው፡፡
Read more: ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ከ2,500 በላይ ተማሪዎች ለ37ኛ ዙር ሊያስመርቅ ነው
- Details
የ2016 ትምህርት ዘመን ማጠቃለያ የወላጆች ቀን በ30/10/2016 ዓ.ም. እሁድ ቀን ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በዋና ግቢ ቴክኖሎጂ ትልቁ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የት/ቤታችን ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች በተባለዉ ቀን፣ ሰዓትና ቦታ እንድትገኙ እያሳሰብን በዕለቱ የተማሪዎች የዓመቱ ሥራ ውጤት መግለጫ ካርድ የሚሰጥ፣ ለቀጣይ ትምህርት ዘመን አቅጣጫ የሚቀመጥበት ውይይት የሚካሄድበትና ውሳኔ የሚተላለፍበት እንዲሁም ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የሚሸለሙ ስለሆነም ሁላችሁም ተገኘታችሁ እንድትታደሙ እንገልጻለን፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ የ2015/16 የሥራ ዘመን መጠናቀቁን ተክትሎ ለ2017/18 ለሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ አዲስ የተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ ሥራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ የሥራ አስፈፃሚዎች ምርጫ ተጠናቀቀ
- Details
አቶ አሰፋ ጨጉልኤ ከአባታቸው ከአቶ ጨጉልኤ ቂዳ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሳባሬ ሳቂሞ በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር በቦንኬ ወረዳ በገረሴ ከተማ በ1966 ዓ/ም ተወለዱ፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 12ኛ ክፍል ተማሪ የአብሥራ ፍፁምና ዳግም ሰለሞን የጋሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከሰኔ 10 – 15/2016 ዓ/ም ባዘጋጀው ዞናዊ የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ላይ የፈጠራ ሥራዎችን በማቅረብ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና ኮሚዩኒቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዕውቅናና የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዞናዊ የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ላይ ተሳተፉ