በአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ‹‹ Hydraulic and Water Resources Engineering›› ፋከልቲ በ‹‹ Hydraulic Engineering›› የትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ክንዴ ዘውዴ የመመረቂያ ጽሑፍ ጥቅምት 15/2018 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል። የመመረቂያ ጽሑፉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
ዕጩ ዶ/ር ክንዴ ዘውዴ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹Soil and Water Engineering›› ያገኘ ሲሆን የ2ኛ ዲግሪውን ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹ Hydraulic Engineering›› አግኝቷል፡፡
ዕጩ ዶ/ር ክንዴ ዘውዴ የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ‹‹ Hydraulic Engineering›› የትምህርት ፕሮግራም ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹Spatiotemporal Dynamics Of Stream flow and Hydro-Climatic Variables in the Upper Omo Gibe Basin Ethiopia›› በሚል ርእስ ሠርቷል፡፡
የዕጩ ዶ/ር ክንደ ዘውዴ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ የሚመረቅ ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

