የፌዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም ከሁሉም ካምፓሶች በተወጣጡ የሥነ ምግባር አምባሳደር ተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢ/ር ቦጋለ ገ/ማርያም ተማሪዎች የተሻለ ውጤትና ሥነ ምግባር በመያዝ ተወዳዳሪና ዩኒቨርሲቲውን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወክሉ እንዲሁም ሀገራቸውን የሚጠቅሙ እንዲሆኑ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ወርቁ እንደገለጹት በኮሚሽኑ መመሪያ መሠረት የሥነ ምግባር አምባሳደርነት ውድድር በማካሄድ የተማሪዎች የሥነ ምግባር ዕጩ አምባሳደር መለየት፣ ተልእኮ መስጠት እና የሥነ ምግባር ግንባታ ንቅናቄ በመፍጠር በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ማፍራት የመርሐ ግብሩ ዋነኛ ዓላማ ነው፡፡
አክለውም ተማሪዎች በሥነ ምግባር አምባሳደር የሚሆኑት ከየካምፓሶች፣ ት/ቤቶችና ኮሌጆች በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያላቸውና በሥነ ምግባራቸው በተቋሙ የተመሰገኑ፣ በንብረት አጠባበቅና አጠቃቀም ላይ መልካም ተሞክሮ ያላቸው እና በተለያዩ ዘርፎች ባላቸው ተሳትፎ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በውድድሩ ከ1-3 ለወጡ ተማሪዎች ጽ/ቤቱ የዕውቅና ምስክር ወረቀት ያበረከተላቸው ሲሆን በቀጣይ በኮሚሽኑ ለሚካሄደው ውድድርም 10 ተማሪዎች ተመልምለዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

