ጥር 2/2016 ዓ/ም ሊከበር የነበረው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ቀን በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ምክንያት ወደ ጥር 6/2016 የተዛወረ በመሆኑ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ይህንን በመረዳት በዕለቱ ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ ከዚህ ቀደም በተጠቀሰው የስብሰባ አዳራሽ ተገኝታችሁ ተሳታፊ እንድትሆኑ ከይቅርታ ጋር ያሳውቃል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ በከፍተኛ ትምህርት የከፍተኛ አመራር ዝግጅት፣ ምልመላና ስምሪት ሥርዓት ማስተግበሪያ መመሪያ መሠረት ለሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ለመመደብ ባካሄደው ውድድር ከቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች መካከል ዶ/ር ደስታ ጋልቻን የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ሆነው እንዲያገለግሉ ከጥር 01/2016 ዓ/ም ጀምሮ ሾሟል፡፡

አርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ‹‹Emerging Digital Technologies for Improved Aquatic Ecosystem Services›› በሚል ርእስ ከስዊድን ሀገር ማልሞ ዩኒቨርሲቲ (Malmo University) ከመጡት ዶ/ር ፍሥሃ መኩሪያ ጋር ታኅሣሥ 25/2016 ዓ/ም   ሴሚናር አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተከናወነ በሚገኘው የከተማ ግብርና ሥራ ውብና ማራኪ አካባቢ ከመፍጠር ባሻገር ሙዝ፣ ፓፓያ፣ ግሽጣና ሌሎች ፍራፍሬዎች ለሽያጭ በማቅረብ ለተቋሙ ተጨማሪ ገቢ እያስገኙ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡