አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል አከባበር ባመረና በደመቀ መንገድ እንዲከበር ከአርባ ምንጭ ከተማ፣ ከጋሞ ዞን፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በትብብር እየሠራ ይገኛል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
በዓሉ የሚከበረው በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዓባያ ካምፓስ ስቴዲየም በመሆኑ ካምፓሱንና ስቴድየሙን ለበዓሉ በሚመጥን መንገድ መሠረታዊ በሆኑ ግብአቶች የማሟላትና ሥፍራውን የማስዋብ ሥራ ዩኒቨርሲቲው ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶች የሚያርፉበትን በዓባያ ካምፓስ የሚገኙ ማረፍያዎችን ጭምር የማደስ፣ የማስዋብና በአስፈላጊው ግብአት የማሟላት ሥራ ተሠርቶ እንግዶችን በመጠባበቅ ላይ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንትና የበዓሉ ዐቢይ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ታሪኳ ወ/መድኅን ገልጸዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ለበዓሉ በድምቀት መከበር የሚጠበቅበትን ሲወጣ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ ዝግጅቱን አጠናቆ እንግዶችን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ዶ/ር ዳምጠው በበዓሉ ለመታደም ወደ አርባ ምንጭ ለሚመጡ የበዓሉ ተሳታፊዎች የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በዓሉ ባማረ ሁኔታና በስኬት እንዲጠናቀቅ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት