በ2014 የትምህርት ዘመን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 1 እና 2 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 3 እና 4 እንዲሁም ትምህርት የሚጀመረው ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ይሆናል፡፡
በመሆኑም ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-
- የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና ኮፒ፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና ኮፒ፣
- የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጂናልና ኮፒ፣
- አራት ፓስፖርት ሳይዝ የሆነ ጉርድ ፎቶ፣
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፣ እንዲሁም
- ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ)
በመያዝ ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ ካምፓሶች የተመደባችሁ በየካምፓሶቻችሁ በሚገኙ የሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን የተመደባችሁበት ካምፓስ መረጃ ከዩኒቨርሰቲው ድህረ-ገጽ www.amu.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንዲሁም ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት