ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ እንኳን ለ8ኛው ዓመት ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያልን “ በህዝቦቿ ተሳትፎ ህዳሴዋን ለማረጋገጥ ሰንደቅ አላማዋን ከፍ ከፍ ለማድረግ እየተጋች ያለች አገር ኢትዮጵያ ” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 8 /2008 ዓ.ም በዋናው ግቢ ከጠዋቱ በ2:30 ጀምሮ ይከበራል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በዕለቱ በመገኘት በዓሉን እንድናከብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!! ማሳሰቢያ፡- ከሌሎች ካምፓሶች ለሚገኙና በዓሉን ለሚታደሙ ዩኒቨርሲቲያችን የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት