አዲስ ለተመደባችሁ መደበኛ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ /መግቢያ ቀናት ከጥቅምት 12-13/ 2009 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም በ12/02/2009 ዓ/ም (ቅዳሜ) ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ መጓጓዣ መኪና ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀ ስለሆነ በተጠቀሰው እለት አዲስ አበባ ክፍለ ሀገር አውቶቡስ ተራ (መርካቶ) በጠዋቱ 12፡00 ሰዓት በመገኘት በአገልግሎቱ እንድትጠቀሙ እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ይደውሉ
- 046 881 4986
- 046 881 3167
- 046 881 0772
መልካም መንገድ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ