በ2016 ዓ/ም በቅድመ-ምረቃ  ከዩኒቨርሲቲው ለተመረቁ  5 ግለሰቦች ነፃ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል  ለመስጠት ተወስኗል፡፡ በመሆኑም ከዩኒቨርሲቲው በ2016 ትምህርት ዘመን በከፍተኛ  ውጤት የተመረቃችሁ እና  ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ዲግሪ መግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ የማለፊያ ሰርተፊኬት የያዛችሁ ተመራቂዎች በዕድሉ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን  ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሥራ ሰዓት የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ውጤት መረጃ እና የሀገር አቀፍ  ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት መግቢያ ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት በመያዝ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና  አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል፡፡