የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለተኛ ሴሚስተር በመደበኛ፣ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቶችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
በማስተርስ ድግሪ በማስተርስ ድግሪ
1. Mathematical Modeling 1. Medical Microbiology
2. Inorganic Chemistry
3. Physical Chemistry
በማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጀ በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ
PhD PhD
1. Disaster Risk Management 1. Animal Nutrition
በማስተርስ ድግሪ በማስተርስ ድግሪ
1. Special Needs 1. Post harvest Technology
2. Teaching Amharic (TEAM) 2. Animal Genetics and Breeding
3. Environment and Sustainable Development 3. Irrigation Agronomy
4. Governance and Development studies
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች
- የትምህርት መረጃ፡- ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ እንዲሁም 3 ጉርድ ፎቶ እና ኦፊሻል ትራንስክሪፕት/ Official Transcript/
- የድጋፍ ደብዳቤ፡- ከመ/ቤት ኃላፊ /ከቀድሞ መምህር/ Recommendation Letter
- የመመዝገቢያ ክፍያ፡- 40 ብር እና የማመልከቻ ቅጽ ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 211 እና ከዩቪርሲቲው ዌብሳይት (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የግል አመልካቾች፡- ከሚሰሩበት መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- በመንግስት /በድርጅት ስፖንሰርነት ለሚማሩ በመስሪያ ቤቱ/በድርጅቱ ኃላፊ የሚፈረም /Sponsor ship form / ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 211 እና ከዩቪርሲቲው ዌብሳይት (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማመልከቻ' የፈተና መስጫ 'የውጤት ማሳወቂያ' የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ
- የማመልከቻ ጊዜ ፡- ከጥር 15/2009 ዓ.ም እስከ የካቲት 10/2009 ዓ.ም
- የማመልከቻ ቦታ ፡-አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ቅበላ ክፍል 211 እና አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት/አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ጎን /
- ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር የሚወጣበት ቀን፡- የካቲት 13/2009 ዓ.ም
- መግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡-የካቲት 16/2009 ዓ.ም
- የምዝገባ ጊዜ ፡- ከመጋቢት 6 እስከ 8 /2009 ዓ.ም
- ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ፡- መጋቢት 11/2009 ዓ.ም
ማሳሰብያ፡- ማንኛውም አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት/ Official Transcript/ በምዝገባ ወቅት ከተማረበት ተቋም ማቅረብ አለበት፡፡
አርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አሉሙናይ ዳ/ጽ/ቤት