በዘንድሮው 39ኛ ዙር የምረቃ መርሃ-ግብር ላይ በሕክምና (Medicine) ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ (First Degree)፣ በሁለተኛ ዲግሪ (Masters) እና በዶክትሬት ዲግሪ (PhD) ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ይመረቃሉ።
ዩኒቨርሲቲው የተመራቂ ተማሪዎችን የስኬት ጉዞ ለመዘከርና ታላቁን የምረቃ በዓል በታቀደው መሠረት ለማካሄድ የሚያስችሉትን አስፈላጊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች እያጠናቀቀ ይገኛል። በዕለቱም የተመራቂ ቤተሰቦች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተገኙበት ደማቅ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ይጠበቃል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፤ ለመላው ተመራቂዎች፣ ለተመራቂ ቤተሰቦችና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! እያለ መልካም የምረቃ በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል!
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ


