ማስታወቂያ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ2012 የትምህርት ዘመን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያለ ለነባርና በ2012 ዓ/ም አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ ቦታና የምዝገባ ጊዜያትን ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት እናሳውቃለን፡፡
የምዝገባ ቀናት
• ነባር 2ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ መደበኛ የቅድመ ምረቃ፣ የድህረ-ምረቃ እና የተከታታይና ርቀት ተማሪዎች ከመስከረም 21-22, 2012 ዓ.ም
• አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ከመስከረም 28-29, 2012 ዓ.ም
• አዲስ ያመለከታችሁ እና የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ የተከታታይና ርቀት ተማሪዎች ከመስከረም 28-29, 2012 ዓ.ም
• አዲስ ያመለከታችሁ እና የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ከመስከረም 28-29, 2012 ዓ.ም
ሪፖርት የማድረጊያ ቦታ
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች……………………… በዋናው ካምፓስ
• የህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ………………………በነጭ ሣር ካምፓስ
• የተፈጥሮ ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ……………………………..……በአባያ ካምፓስ
• የግብርና ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ………………………………………በኩልፎ ካምፓስ
• የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም የማህበራዊ ሣይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ተማሪዎች………በጫሞ ካምፓስ
• የፔዳጎጂ እና ብሄቨየራል ሳይንስ እንዲሁም የህግ ት/ቤት ተማሪዎች …………….………… በጫሞ ካምፓስ
• የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች ……………………………………………………………………………………… በሳውላ ካምፓሰ
ማሳሰቢያ፡ አዲስ የተመደባችሁ የዩኒቨርስቲው የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ወቅት
• የመሰናዶ ትምህርት(11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ትራንስክሪፕት ዋናውን ከ 2 ኮፒ ጋር
• የ10 እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውን ከ 2 ኮፒ ጋር
• ሦስት በአራት የሆነ 4(አራት) ጉርድ ፎቶግራፍ
• እንዲሁም ለግል መገልገያ የሚሆን እንደ አንሶላ ፤ትራስ ልብስ ፤ የስፖርት ትጥቅና የመሣሰሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኃል፡፡
• ተማሪዎች በየካምፓሶቻችሁ በተጠራችሁበት ቀናት ሪፖርት እንድታደርጉ እያሣሰብን ቀደም ብለው ወይም ዘግይተው ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት እንደማይሰጣቸው ያስታውቃል፡፡
• ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፈው በሚመጡ ተማሪዎች ላይ ለሚደርሰው መጉላላት ዩኒቨርሲቲው ተጠያቂ አይሆንም፡፡
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አ/ዳ/ጽ/ቤት