ከቀን 26/3/2015 ዓ/ም ጀምሮ  በዩኒቨርሲቲው  የመማር  ማስተማር  ሥራ  በተሟላ  ሁኔታ  እየተከናወነ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡  በዚህም  ምክንያት የዓመቱ  የትምህርት ጊዜ እየባከነ በመሆኑ ጉዳዩን  አስመልክቶ በየደረጃው  ካሉ የዩኒቨርሲቲው አመራር አካላት ጋር በተደረጉ ውይይቶች በዩኒቨርሲቲው  የመማር ማስተማር ሥራው እየተከናወነ የመምህራን ጥያቄዎችን  ከሚመለከታቸው  አካላት  ጋር  በመሆን  ማስቀጠል  እንደሚቻል  ታምኖበታል፡፡  ስለሆነም ከ30/3/2015 ዓ/ም ጀምሮ  ሁሉም  በሥራ  ላይ  ያላችሁ  (በትምህርት ላይ ያልሆናችሁ)  መምህራን   በመደበኛ  ሥራችሁ  ላይ እንድትገኙ  ዩኒቨርሲቲው  ያሳስባል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ