የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂክ ዕቅድ ክትትልና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የ2016 በጀት ዓመት የ12 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም አቅርቦ ተገምግሟል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለ2017 ዓ/ም ዕቅድ ዝግጅት እንደመነሻ የሚያገለግል መሆኑን ገልጸው ሁሉም የትምህርትና የሥራ ክፍሎች የ2017 ዕቅዶቻቸውን ከዚሁ መነሻ እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ሪፖርቶች በአንድ ሰው ተዘጋጅተው ወደሚመለከተው የበላይ ኃላፊ ከመላካቸው በፊት በዘርፉ ሠራተኞች መገምገም እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክ ዕቅድ ክትትልና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ሰለሞን ይፍሩ ሪፖርቱን በቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት የትምህርት ጥራት፣ አግባብነትና ተደራሽነትን ማረጋገጥ፣ የምርምር እና ፈጠራ ሥረዎች ተደራሽነትና  ፍትሐዊነት እንዲሁም የሀገር በቀል ዕውቀትን ማጣጣምና ማሳደግ፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት እና የሳይንስ ባህል ግንባታ ተደራሽነትንና ፍትሐዊነትን ማሳደግ፣ የተቋማት ትስስርና ተሳትፎ፣ ሥራ ፈጠራ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ማሳደግ፣ የትምህርት አመራርና አስተዳደርን ማጠናከር፣ የትምህርት ተቋማዊ አቅምና ብቃትን ማጎልበት፣ የትምህርት መሠረተ ልማትና ፋሲሊቲ ማሳደግ እና የሀብት ምንጭና አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሳደግ በሚሉ ግቦች በዓመቱ የተከናወኑትን ዋና ዋና ተግባራት አቅርበው በካውንስሉ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው በየዘርፉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ማብራሪያዎች ተሰጥተው ዓመታዊ ሪፖርቱ ጸድቋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት