የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤት በ2017 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትነው የሚያልፉ አመልካቾችን ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡


የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ በተመለከተ፡-

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የNGAT ምዝገባ የሚካሄደው ከሐምሌ 24 - ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ
በ https://NGAT.ethernet.edu.et የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ፕሮግራሞችንና የማመልከቻ ሂደት በተመለከተ፡-

የድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤት በ2017 የትምህርት ዘመን ለመማር ማመልከቻ ሂደት የሚከናወነው በመረጃ መረብ (Online) ከታች የቀረበውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ወይም በዌብ ፔጅ ላይ ማስፈንጠሪያውን በማስገባት መጠይቆችን በአግባቡ በመሙላትና የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በማያያዝ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ያገኛሉ፡፡ NGAT ፈተና ያለፉ አመልካቾች የማመልከቻ ጊዜ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ መረጃዎች ባግባቡ ካልተሞሉ ማመልከቻው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ለማመልከት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ https://forms.gle/zPTTETT49DbdVv4QA

NGAT ፈተና ያለፉ አመልካቾች በአካል ማቅረብ የሚጠበቅባቸው መረጃዎች፡-

1. የትምህርት መረጃ፡- ሙሉ የትምህርት ማስረጃ ኦርጅናልና ሁለት (2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት (2) ጉርድ ፎቶግራፍ
2. የድጋፍ ደብዳቤ፡- የአመልካቹን ጥንካሬ እና ባህሪ የሚገልጽ ደብዳቤ ከመ/ቤት ኃላፊ ወይም ከቀድሞ መምህር
3. የመመዝገቢያ ክፍያ፡- የመመዝገቢያ ብር 100 ገቢ የተደረገበትን የባንክ ስሊፕ ወደ ደረሰኝ በማስቀየርና በመያዝ፣ የማመልከቻ ቅጽ በመሙላትና ማቅረብ
4. በመንግሥት ወይም በድርጅት ስፖንሰርነት ለሚማሩ በመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ የተፈረመ ስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማሳሰብያ፡-

 መደበኛ የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ሁሉም በተመጣጣኝ ክፊያ የዶርም አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ምርምራቸውን የሚያካሂዱበት በዩኒቨርሲቲው ምርምር መመሪያ መሠረት የፋይናንስ ድጋፍ ያገኛሉ፡፡
 የማመልከቻ ቅጽ ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና ከዩኒቨርሲቲው ድረ ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡ ክፍያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000021480502 መፈጸም ይቻላል፡፡
 የስፖንሰርሺፕ ቅጽ ከዩኒቨርሲቲው ድረ ገፅ www.amu.edu.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
 ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ/ች አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ቢቻል በምዝገባ ወቅት ካልሆነ በ30 ቀናት ውስጥ ካላቀረበ/ች ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት