የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቅ ዶ/ር ምግባር አሰፋ በቁጥር 52 መጻሕፍትን ለዩኒቨርሲቲው በስጦታ አበርክተዋል፡፡ መጻሕፍቱ በምኅንድስና ዘርፍ ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች እገዛ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪና ምሩቅ ዶ/ር ምግባር አሰፋ ለተማረበት ዩኒቨርሲቲ በማሳብ በዚህ ልክ ድጋፍ ማድረጋቸው የትልቅነት ማሳያ እንዲሁም ለሌሎች የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃን አርኣያ የሚሆን ተግባር ነው ብለዋል፡፡
የቤተ መጻሕፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል በበኩላቸው በስጦታ የተበረከቱት መጻሕፍት በዘርፉ ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች በእጅጉ የሚጠቅሙና በዘርፉ ያለውን የመጻሕፍት እጥረት የሚቀርፉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ዶ/ር ምግባር አሰፋ በዩኒቨርሲቲው ሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ት/ክፍል በመማርና በማስተማር ጭምር ያገለገሉ ሲሆን አሁን ላይ ቦትስዋና በሚትባለው የአፍሪካ ሀገር በማስተማር ሙያ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ምሁር ናቸው፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት