ኃይሌ ሪዞርት አርባ ምንጭ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች ጥቅምት 1/2017 ዓ/ም የንጽሕና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የኃይሌ ሪዞርት አርባ ምንጭ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት ታሪኩ ድርጅቱ በተለያዩ መንገዶች ላለፉት ሦስት ዓመታት የአካባቢውን ማኅበረሰብ ሲደግፍ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ ድርጅታቸው 70 ካርቶን የንጽሕና መጠበቂያ በድጋፍ መልክ ያቀረበ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ ይህም በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት የንጽሕና መጠበቂያ እጥረት የሚገጥማቸው ሴት ተማሪዎች እንዳይቸገሩ እንዲሁም ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጎሉ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኃይሌ ሪዞርት በቀጣይም መሰል ድጋፎችን ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡

የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪ ወ/ሮ አበበች አዳነ እና የዋናው ካምፓስ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ማርሸት ማቴዎስ ድጋፉ በንጽሕና መጠበቂያ እጥረት ለሚችገሩ ተማሪዎች ትርጉሙ ቀላል እንዳልሆነ በመግለጽ በተቋሙ፣ በሥራ ክፍሉና በድጋፉ ተጠቃሚ ሴቶች ስም ለኃይሌ ሪዞርት አርባ ምንጭ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት