አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ‹‹ሕሊና የልጃገረዶች ማብቃት ፕሮግራም›› ጋር በመተባበር አፍሪካ ኢምፓወርመንት ዩኬ ‹‹Africa Empowerment UK›› በተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች ታጥቦ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የንጽሕና መጠበቂያ ድጋፍ ጥቅምት 12/2017 ዓ/ም አድርጓል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የ‹‹አጅየት ፓድስ›› መሥራችና ማኔጀር ወ/ሪት ሕሊና ተክሌ እንደገለጹት ‹‹ሕሊና የልጃገረዶች ማብቃት ፕሮግራም›› በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚካሄድና እንደ ጅምር ከተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲው የሥራ ባለድርሻዎች ጋር የመተዋወቅ፣ ስለ ወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ ግንዛቤ የመፍጠርና የንጽሕና መጠበቂያ ድጋፍ የማድረግ መርሃ ግብር ነው፡፡ ከ450 በላይ ለሚሆኑ ሴት ተማሪዎች የሚሆን ከሦስት መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የንጽሕና መጠበቂያ ምርት ማምጣታቸውን የገለጹት ወ/ሪት ሕሊና ቀጣይነት ያለው ፕሮጀክት በመዘርጋትና የማምረቻ ማሽን በማቅረብ ታጥቦ በድጋሚ ለጥቅም የሚውል የንጽሕና መጠበቂያ ዩኒቨርሲቲው በራሱ ማምረት የሚጀምርበትን መንገድ ማመቻቸት በዕቅድ መያዙን ገልጸዋል፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ሠናይት ሳህሌ ለተደረገው ድጋፍ በሥራ ክፍላቸውና የድጋፉ ተጠቃሚ በሆኑ ሴት ተማሪዎች ስም አመስግነዋል፡፡
የንጽሕና መጠበቂያው ለሁለት ዓመት ስለሚያገለግል የምናወጣውን ወጪ ያስቀርልናል ያለችው የ3ኛ ዓመት የአርክቴክቸር ተማሪ ዳናዊት መኑ ከጤና አኳያም ስጋት የሌለበት መሆኑ ይበልጥ እንዳስደሰታት ተናግራለች፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት