የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ ከሰው ኃብት ልማት ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመተባባር ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች የህይወት ክሂሎት ሥልጠና መጋቢት 27/2017 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ከሥልጠናው ባሻገርም ሴት የምክር ቤት አባላት የተከበሩ ወ/ሮ መሠረት ሐይሌ የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ረዳት የመንግሥት ተጠሪ እና የተከበሩ ወ/ሮ በየነች ደመቀ የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዩች ምከር ቤት አባል እና የሰው ኃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል የሕይወት ተሞክሮአቸውን ለተማሪዎች አካፈለዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ጉዳዮች  ምክትል ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጳውሎስ ታደሰ የአንድ ሀገር ልማት እና ብልጽግና ሊረጋገጥ የሚችለው ሁሉም ዜጎች በሁሉም ዘርፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ሲሆን ለዚህም መሳካት የሥርዓተ-ጾታ ጉዳይ ሥራዎች ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል፡፡ ይህን ለማሳካት በመንግሥት የተለያዩ ስትራቴጂዎች ተቀይሰው አመርቂ ሥራዎች እየተተገበሩ እንደሚገኙ የጠቀሱት ም/ፕሬዝደንቱ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም በተለይ ለሴት ተማሪዎች ትኩረት በመስጠት ሴቶች በትምህርታቸው የተሻለ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲገኙ  የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‹‹Brake Through Trading Share Company›› በተሰኘ ድርጅት ውስጥ የግል ሰብእና ግንባታ ባለሙያ አስልጣኝ አቶ መስፍን መካሻ  ‹‹Goal setting, Time Management and Designing Your Future›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ሥልጠና የሰጡ ሲሆን ሥልጠናው ሴቶች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ባለ ራዕይ ሆነው፣ ራዕያቸውን አውቀው፣ ግብ ቀርጸው ጊዜያቸውን በአግባቡ ተጠቅመው ውጤታማ በመሆን ለሀገር ግንባታና ልማት የበኩላቸውን  አስዋጽኦ እንዲያበረክቱ  የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

 

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

 

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

 

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ /ቤት