አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት እና ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በመተባባር  የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ “The Grand Renaissance Dam: A Decade of Struggle, Lessons, and a New Horizon”  በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ አገር አቀፍ ዐውደ ጥናት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጳጉሜ 1/2017 / ተካሂዷል። 0ውደ ጥናቱ የግድቡን መጠናቀቅ በተመለከተ የተዘጋጀው የሕዳሴ ሳምንት ክብረ በዓል አካል ነው። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / / አብደላ ከማል የሁላችን አሻራ ያረፈበት፣ የድል አድራጊነት ምልክት፣ ሁለተኛ አድዋ የሆነው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ለመላው ኢትዮጵያውያን እጅግ የተለየ ሁነት መሆኑን ተናግረዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ጽናት አንድነትና ቁርጠኝነት የታየበት ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ዕውቀት፣ ገንዘብና አቅም ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫናን ጭምር  በመቋቋም የሰሩት ከራስ አልፎ ለሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጭምር የሚተርፍ ትልቅ አሻራ መሆኑንም ተናግረዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ 5150 ሜጋ ዋት የመብራት ኃይል በማመንጨት ሀገራችን ያላትን ኃይል የማመንጨት አቅም ከእጥፍ በላይ በማሳደግ 45 ከመቶ የሚሆነው ህዝባችንን  የኤሌክትሪክ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነውም ብለዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በውኃው ምኀንድስና ዘርፍ ቀዳሚ የሀገራችን የልህቀት ማዕከል መሆኑን ያነሱት / / አብደላ የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በሌሎች መሰል ፕሮጀክቶች ላይ የሰሩ በርካታ መኀንዲሶችን በማፍራት የበኩሉን ድርሻ የተወጣ መሆኑንም አንስተዋል። በግድቡ ግንባታ ወቅት ዩኒቨርሲቲው በቦንድ ግዥ፣ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት የበኩሉን ሲወጣ ቆይቷል ያሉት ፕሬዝደንቱ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም ግድቡ ረዥም አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችሉ ከግድቡ ደህንነትና ከአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች ጋር የተገናኙ ተግባራትን ያከናውናል ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር / አብዲ ዘነበ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ኃብት የታደለች፣  ያላት የተፈጥሮ ኃብት ከራሷ አልፎ ለሌሎች ሀገራት መትርፍ የሚችል ይህን ኃብት ማልማትና ጥቅም ላይ ማዋል ለቀጠናዊ ትብብርና ትስስር ቁልፍ መሳሪያ ሆኖ ማገልግል የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል። በኃይል ዘርፍ ብቻ 60 ሺህ ሜጋ ዋት ከታዳሽ ኃይል የማመንጨት አቅም  አለን ያሉት / አብዲ ሆኖም በተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ጫናዎች ምክንያት መሰል ፀጋዎችን አልምቶ በመጠቀም ረገድ ድክመቶች መኖራቸውን አንስተዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ 2003 / መጀመር በርካታ አሉታዊ ቀንበሮች መሰበር የጀመሩበት ወቅት ነው ያሉት /ዋና ዳይሬክተሩ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተገኘውን ትልቅ ድል በሌሎች ዘርፎችም መድገም እንደሚገባ በአጽንዖት ተናግረዋል። አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራር በመሆን እንዲሁም በሙያቸውም ከፍተኛ አስተዋጽኣ ያበረከቱ በርካታ ባለሙያዎችን ያፈራ አንጋፋ ተቋም መሆኑንም / አብዲ በንግግራቸው አንስተዋል።

የታላቁ ሕዳሴ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ /ቤት ጄኔራል ዳይሬክተር / አረጋዊ በርሄ በበኩላቸው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሕዝብና መንግሥት ከተባበረና ከተቀናጀ መሰል ታላላቅ በሀገርና ሕዝብ ላይ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ሥራዎችን መሥራት እንደሚቻል ያሳየ ተምሳሌታዊ ፕሮጀክት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያውያን በራሳችን አቅም በአፍሪካ ግዙፉን ግድብ መገንባታ መቻላችን በራስ አቅም ማደግና መብልጸግ እንደሚቻል በተግባር ያየንበት እንዲሁም በሀገርና ሕዝብ ዘንድ የእንችላለን መንፈስን ያሰረፀ ሀገራዊ ፕሮጀክት መሆኑንም አስረድተዋል። ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሚመነጨው የኤክትሪክ ኃይል እንደ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ኬንያ ላሉ ሀገራት ጭምር የሚተርፍ ነው ያሉት / አረጋዊ ይህም ቀጣናዊ ትብብርንና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑንም አስረድተዋል።

የብሔራዊ ኤክስፐርቶች ቡድን እና  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተደራዳሪ ኮሚቴ ቴክኒክ ቡድን ሰብሳቢ / ጌዲዮን አስፋው  በአባይ ወንዝና ከሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ ከታችኛው  ተፋሰስ ሀገራት ጋር ሲካሄዱ በነበሩ የውይይት እና የድርድር ሂደትን አስመልክት በኣንላይን ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን በገለጻቸው ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ሥራ መጠናቀቅ ባሻገር የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ውጤቶችን ባለፉት ዓመታት ማስመዝገቧን ተናግረዋል። እንደ / ጌዲዮን ገለጻ .. 2015 በሶስት መሪዎች ደረጃ የተፈረመው "Declaration of Principles" በመባል የሚታወቀው ስምምነት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ የቀረበው ተደጋጋሚ ክስ ውድቅ እንዲሆን በማድረግ ጉዳዩ በአፍሪካ ሕብረት ደረጃ እንዲፈታ መወሰኑ ከተመዝገቡ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች መካከል መሆናቸውን ገልጸዋል።

የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር / ታምሩ ተሰሜ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ኃብት የተገነባ፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አንድነት፣ መስዋዕትንት እና ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ የሉዓላዊነት ምልክት እና ከግንባታ በላይ የሆነ ፕሮጀክት እንደሆነ አመላክተዋል። ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል እና ዘላቂ ልማት ውስጥ ያላትን ቀጣናዊ የመሪነት ሚና የሚያጠናክር ነውም ብለዋል። በውኃው ዘርፍ ባለፉት 40 ዓመታት ሲሰራ ለቆየው የያኔው የአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለአሁኑ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኩራት እና ከፍተኛ መነሳሳት የሚፈጥር እንደሆነም / ታምሩ በንግግራቸው አንስተዋል።

በዐውደ ጥናቱ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት ወቅት የነበሩ ትግሎች፣ የተመዘገቡ ድሎች፣ ከውኃ  ዲፕሎማሲ አንጻር የተገኙ ትምህርቶች እንዲሁም ለአካባቢው ትብብር የሚከፈቱ አዳዲስ ዕድሎች ጋር የተገናኙ የውውይት መነሻ ጽሑፎች በየዘርፉ ምሁራን ቀርበው ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን በዕለቱ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና  የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነትም ተፈራርመዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ /ቤት