የሁሉም ተማሪዎች የሬጅስትራርና አሉምናይ ፋይል መሠረታዊ መረጃዎችን መያዝ እንዳለበት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች (ሪሚዲያል፣ ቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ) የምትገኙ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆናችሁ ተማሪዎች፣ እስከ ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚከተሉትን መረጃዎች በዩኒቨርሲቲው የኤስ.ኤም.አይ.ኤስ (SMIS) ሥርዓት ውስጥ እንድታስገቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡-
- የፋይዳ (Digital ID) ፋን ቁጥር
- የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ቁጥር
- የአማርኛ ስም (ከነ አያት)
- የትውልድ ዘመን (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር)
ማሳሰቢያ፡- ይህንን መረጃ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማታጠናቅቁ ተማሪዎች፣ በቀጣይ በምረቃ ሂደትም ሆነ በሌሎች የሬጅስትራር አገልግሎቶች ላይ ለሚፈጠሩ ክፍተቶች ዩኒቨርሲቲው ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት


