የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በ25/12/2012 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር በመደበኛ፣ በክረምት፣ በሳምንት መጨረሻ እና በተከታታይና ርቀት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 2,300 በላይ ተማሪዎች ቅዳሜ ነሐሴ 30/12/2012 ዓ/ም እንዲመረቁ ወስኗል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 503ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የሚካሄደው ሥነ-ሥርዓት በዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ እና የዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን በቅርብ የሚገኙ ጥቂት ተመራቂ ተማሪዎች በዋናው ግቢ አዳራሽ በአካል በመገኘት ይሳተፋሉ፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጋሞ ዞን አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ም/ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በክብር እንግድነት፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባና የዩኒቨርሲቲው አልሙናይ ፕሬዝደንት አቶ ኤርምያስ ዓለሙ፣ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ፕ/ር ገብሬ ኢንቲሶ እንዲሁም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች ይገኛሉ፡፡
በተጨማሪም ሴኔቱ ለ6 ነባር የዩኒቨርሲቲው መ/ራን፡- ለዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ፣ ዶ/ር ስምዖን ሽብሩ፣ ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ፣ ዶ/ር ታምሩ ሽብሩ፣ ዶ/ር ክንፈ ካሳ እና ወ/ሮ ጊስታኔ አየለ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት js