አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2009 የትምህርት ዘመን 6125 አዲስ ተማሪዎችን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለማስተማር ተቀብሏል፡፡ የቅበላ መጠኑ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር ብልጫ ያለው ሲሆን ከአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ 2634ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
ተማሪዎቹ በአገልግሎት አቅርቦትም ሆነ በዩኒቨርሲቲው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ችግሮች እንዳይገጥማቸው አስቀድሞ የተለያዩ ኮሚቴዎችና ንዑስ ኮሚቴዎችን በማዋቀር በቂ ቅድመ-ዝግጅት መደረጉን የተማሪዎች አገልግሎት ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ጳውሎስ ታደሰ ገልፀዋል፡፡
በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ በሠላም ፎረም፣ በተማሪዎች ህብረት፣ በነባር ተማሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዉ ትራፊክ ፖሊስ፣ በትራንስፖርትና ስምሪት እና በፀጥታና ደህንነት ክፍሎች ቅንጅት በዋናው ግቢ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በመኝታ አገልግሎት በኩል ጥቂት ክፍተቶች የታዩ ቢሆንም ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመሆን አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት ተችሏል፡፡
ተማሪዎቹ በየተመደቡበት ካምፓሶች በመገኘት በስነ-ምግባር መመሪያ፣ ዩኒቨርሲቲው በሚሰጣቸው አገልግሎቶች፣ በመማር ማስተማር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ገፅታ ላይ በሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ የትምህርት ክፍል መረጣ በማከናወንም ‹የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ› መርህን ለማሳካት በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡
ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት በዩኒቨርሲቲው የተደረገላቸው አቀባበል ያስደሰታቸው መሆኑን በመግለጽ የመጡበትን የትምህርት ዓላማ ያሳኩ ዘንድ መምህራንና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከጎናቸው በመቆም ሀገራዊ ኃላፊነታቸው እንዲወጡ ጠይቀዋል ሲል፡፡