
- Details
የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከል ከጋሞ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ጋርና ከደረጃ ዶት ኮም/Dereja.Com Academy/ ከተባለ የግል ድርጅት ጋር በመተባባር ለአርባ ምንጭ ከተማ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ስለደረጃ ዶት ኮም አካዳሚ አክስለሬተር ፕሮግራም/Dereja.Com Academy Accelerator Program/ ሥልጠና ከኅዳር 3/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ወራት እየሰጠ ነው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝት ማስ/ጽ/ቤት እና የዩኒቨርሲቲው ባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋም ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን እና ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ባህል፣ ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ እንዲሁም ከጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ‹‹የሙዚየም አደረጃጀት፣ አገልግሎት አሠጣጥና ተደራሽነት›› በሚል መሪ ቃል በደቡብ ክልል ካሉ ዞኖች ለተወጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከኅዳር 5-6/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በደቡብ ክልል ለሚገኙ የቱሪዝም ባለሙያዎችና አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከጋሞ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያና ደረጃ ዶት ኮም/Dereja.Com/ ከተሰኘ የግል ድርጀት ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2013 እና 2014 ዓ/ም ተመርቀው ሥራ በማፈላለግ ላይ ለሚገኙ ወጣቶች በሥራ ዝግጁነት /Job Readiness/ ዙሪያ ኅዳር 7/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ሥራ በማፈላለግ ላይ ለሚገኙ የአርባ ምንጭ ከተማ ሥራ አጥ ወጣቶች በሥራ ዝግጁነት/Job Readiness/ ላይ ሥልጠና ተሰጠ

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የማኅረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አማካኝነት በምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርገው የተዘጋጁ 10 ንድፈ-ሃሳቦች ቀርበው ኅዳር 9 እና 12/2015 ዓ/ም ግምገማ ተካሂዶባቸዋል፡፡ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስዊዘርላንድ ሀገር ከሚገኘው ኢት-ዙሪች/ETH-Zurich/ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ገጠርንና ከተማን በንጥረ ነገር ዕሴት ሠንሰለት በሚያስተሳስር “RUNRES/ረንረስ” በተሰኘ ፕሮጀክት በአርባ ምንጭ ከተማና ዙሪያዋ ባሉት የገጠር ቀበሌያት ላይ የተለያዩ ተግባራትን ሲሠራ ቆይቶ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ በመጠናቀቁ የሥራዎቹን አፈጻጸም እና የፕሮጀክቱን 2ኛ ምዕራፍ ዕቅድና ትግበራ አቅጣጫዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ኅዳር 03/2015 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በ“RUNRES/ረንረስ” ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2ኛ ምዕራፍ ዕቅድና የትግበራ አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሄደ