
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሂሳብ ት/ክፍል በ“Operation Research” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ ፀጋዬ ነገ ቅዳሜ ኅዳር 03/2015 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በዓባያ ካምፓስ በፒ.ኤች.ዲ. አዳራሽ እንዲሁም በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በማኔጅመንት ት/ክፍል በ“Marketing Management” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ስንታየሁ አሰፋ ረቡዕ ኅዳር 7/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ የመመረቂያ ፅሑፎቻቸውን በማቅረብ የሚያስገመግሙ ይሆናል፡፡ በመድረኩም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች ይገኙበታል፡፡

- Details
ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ለተወጣጡ የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክተሮችና የሲስተም አስተዳደር ባለሙያዎች ‹‹Federated Identity System and Educational Roaming›› በሚል ርዕስ ከጥቅምት 24-26/2015 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክተሮችና የሲስተም አስተዳደር ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጠ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ19/12/2ዐ14 ዓ.ም በምክትል ፕሬዝደንትነት ማዕረግ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር አወዳድሮ ለመሰየም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች ዝቅተኛውን መስፈርት በማሟላት በመመሪያው መሠረት ከስር በስም የተገለጻችሁ ተወዳዳሪዎች ኅዳር 6/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለሚከናወነው ፓናል ኢንተርቪው እና ስትራቴጅክ ዕቅድ ገለፃ የተመረጣችሁ በመሆኑ በስም ዝርዝሩ ቅደም ተከተል መሠረት በተከታታይ ስለምታቀርቡ በተጠቀሰው ቀን በአዲሱ የስብሰባ አዳራሽ በሰዓቱ እንድትገኙ እናስታውቃለን፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ19/12/2ዐ14 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝደንት አወዳድሮ ለመሰየም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች ዝቅተኛውን መስፈርት በማሟላት በመመሪያው መሠረት ከስር በስም የተገለጻችሁ ተወዳዳሪዎች ኅዳር 5/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለሚከናወነው ፓናል ኢንተርቪው እና ስትራቴጅክ ዕቅድ ገለፃ የተመረጣችሁ በመሆኑ በስም ዝርዝሩ ቅደም ተከተል መሠረት በተከታታይ ስለምታቀርቡ በተጠቀሰው ቀን በአዲሱ የስብሰባ አዳራሽ በሰዓቱ እንድትገኙ እናስታውቃለን፡፡
- Details
የአፍሪካ ወጣቶች ወር በአፍሪካ ደረጃ “Breaking the Barriers to Meaningful Youth Participation and Inclusion in Advocacy” በሚል መሪ ቃል ከኖቨምበር 01/2022 እ.ኤ.አ ጀምሮ እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን በሀገራችን ደግሞ በነገው ዕለት ከጧቱ 02፡30 ጀምሮ በዋናው ግቢ በሚገኘው ትልቁ አዳራሽ “ንቁ የወጣቶች ተሳትፎና ተካታችነት ለስብዕና ልማት” በሚል መሪ ቃል ለ16ኛ ጊዜ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የወጣቱን ግንዛቤ፣ ተሳትፎና ስብዕና በሚገነባ መልኩ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች የሚከበር ይሆናል፡፡ በልዩ ትኩረት በትምህርትና ስብዕና ልማት፣ ወጣትና ሥራ ፈጣሪነት፣ የወጣቶች ተዋልዶ ጤናና ስብዕና ልማት እና አደንዛዥ ዕጽ በወጣቶች ስብዕና ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖና ሌሎችም የውይይት ጉዳዮች የተካተቱበት ይሆናል፡፡
- AMU congratulates and applauds to Pal Mai Deng on his current government appointment as Water Resources & Irrigation Minister of the Republic of South Sudan
- በሳሙና ማምረት ላይ ለተደራጁ 6 ማኅበራት ከ7 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ
- የእጩ ዶ/ር ተመስገን ዲንጋሞ የፒ ኤች ዲ (PhD) መመረቂያ ጽሑፍ ተገመገመ
- ለአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች በወባ በሽታ ምርመራና ሕክምና አሰጣጥ አዳዲስ አሠራሮች ላይ ሥልጠና ተሰጠ