
- Details
Arba Minch University congratulates and wishes all the best to Pal Mai Deng, AMU post graduate Masters of Business Administration (MBA) 1st year foreign student, on his current government appointment as the Minister for Water Resources and Irrigation in the Republic of South Sudan. He is one of the foreign students who got Master’s Degree Scholarship in MBA program and joined Arba Minch University in the year 2021. To See more Pictures Click here.

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝት ማ/ጽ/ቤት በአርባ ምንጭ ከተማ እና አጎራባች ቀበሌያት በፈሳሽና ደረቅ ሳሙና አዘገጃጀት ሥራ ላይ ለተደራጁ 6 ማኅበራት ለሥራው የሚያግዙ የአላቂና ቋሚ ቁሳቁስ ድጋፍ ጥቅምት 17/2015 ዓ/ም አድርጓል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በሳሙና ማምረት ላይ ለተደራጁ 6 ማኅበራት ከ7 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ትምህርት ክፍል «Bio Diversity Conservation and Management» ትምህርት ፕሮግራም ላላፉት 5 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት እጩ ዶ/ር ተመስገን ዲንጋሞ የምርምር ሥራቸውን ጥቅምት 21/2015 ዓ/ም የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርበው ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ማዕከል ማስ/ጽ/ቤት ከአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ከሆስፒታሉ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች በወባ በሽታ ምርመራና ሕክምና አሰጣጥ አዳዲስ አሠራሮች ዙሪያ ከጥቅምት 18-19/2015 ዓ/ም የሁለት ቀናት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ለአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች በወባ በሽታ ምርመራና ሕክምና አሰጣጥ አዳዲስ አሠራሮች ላይ ሥልጠና ተሰጠ

- Details
የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ በ2014 በጀት ዓመት ያካሄደውን የማዕድን ሀብት አለኝታ ጥናት ውጤት የክልሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ማዕድንና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን እንዲሁም የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ጥቅምት 17/2014 ዓ.ም ይፋ አድርጓል። ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የማዕድን ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን አበርክቶ ከፍ ለማድረግ በትኩረት መሥራት ይገባል ተባለ