
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ኤይድ/Christian Aid /ከተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በካምባ ወረዳ ዲንጋሞ ቀበሌ ማይጸሌ ወንዝ ላይ አነስተኛ የኃይል ማመንጫ ለማስገንባት ሰኔ 12/2014 ዓ/ም የመሠረት ድንጋይ አስቀምጧል፡፡ ለሥራው ማስፈፀሚያ የሚሆነው ገንዘብ 1.1 ሚሊየን ብር በዩኒቨርሲቲውና 6.123 ሚሊየን ብር በክርስቲያን ኤይድ ግብረ ሠናይ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከክርስቲያን ኤይድ/Christian Aid/ ጋር በመተባበር በካምባ ወረዳ አነስተኛ የውሃ ኃይል ማመንጫ ሊያስገነባ ነው

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን የተገኘ የምርምር ውጤት ላይ ተመሥርቶ ኮሌጁ ከዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት፣ ከጃኖ ዕደ ጥበብ ኢንተርፕራይዝ እና ከGIZ ጋር በመተባበር በጨንቻ ዶኮ ማሾ ቀበሌ ለሚኖሩ ሸማኔዎች የዘመናዊ ሽመና አሠራር ላይ ከግንቦት 20 - ሰኔ 04/2014 ዓ/ም ለ15 ተከታታይ ቀናት የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
Read more: ለጨንቻ ወረዳ ዶኮ ማሾ ቀበሌ ሸማኔዎች የዘመናዊ ሽመና ማሽን የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰጠ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሥራ ላይ ልምምድ የቆዩ የኮሌጁ መምህራንን ሪፖርት ሰኔ 04/2014 ዓ/ም ገምግሟል፡፡ በዕለቱ ከመንግሥትና ከግል ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችል የስምምነት መግባቢያ ሰነድም ተፈራርሟል፡፡
Read more: በሥራ ላይ ልምምድ የቆዩ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን ሪፖርት ተገመገመ
- Details
ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ የክረምት መርሃ-ግብር ተማሪዎች በሙለ
የ2014 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ምዝገባ ሐምሌ 4-5/2014 ዓ.ም ስለሚካሄድ በተጠቀሱት ቀናት
በየካምፓሶቻችሁ ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እየገለጽን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን
ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ እንዲሁም ይህ ማስታወቂያ የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን
የማይመለከት መሆኑን ያስታውቃል፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ