
- Details
በ17/08/2016 ከ8:00 ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በኢንተርፕርነርሽፕ ዙሪያ ያተኮረ ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል። በዝግጅቱ ላይ ታዋቂው የቢዝነስ አማካሪ እና ደራሲ ዶ/ር ወሮታው በዛብህ ተገኝተው የኢንተርፕርነርሽፕ የተግባር ተሞክሯቸውን ያካፍላሉ። በተጨማሪ በዕለቱ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ይካሄዳል። የተሻለ ሃሳብ ያቀረቡ ተማሪዎችም ይሸለማሉ:: ስለሆነም ሁሉም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዚህ ሁነት ላይ እንድትገኙ የተጋበዛችሁ መሆኑን እናሳውቃለን።

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ በደቡብ ኦሞ ዞን ያንጋቶም ወረዳ በሚነገረው የኩዌጉ ቋንቋና ባህል ስነዳ እና ትንተና ላይ ጥናት ለማካሄድ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሚያዝያ 12/2016 ዓ/ም የፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የኩዌጉ ቋንቋና ባህል ስነዳ እና ትንተና ላይ ጥናት ለማካሄድ የመክፈቻ መርሃ ግብር ተካሄደ

- Details
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ማስ/ጽ/ቤት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት እና ከጋሞ ዞን ጋር በመተባበር የግድቡ ግንባታ የተጀመረበት 13ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ «የአባይ ዘመን ትውልድ ታላቅ የሥነ ጽሑፍ ምሽት» “በኅብረት ችለናል!” በሚል መሪ ቃል ግንቦት 09/2016 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ያካሂዳል፡፡ በዕለቱ መርሃ ግብር ላይ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ላይ ያተኮሩ ግጥሞችንና አጭር ትውን ተውኔቶችን ማቅረብ የምትችሉ ተማሪዎች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻችሁን ዩኒቨርሲቲው አወዳድሮ ከ1ኛ - 3ኛ የወጡ የተማሪዎች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች በመድረኩ እንዲቀርቡ ዕድል ለመስጠት ስለተፈለገ ከሚያዝያ 15-30/2016 ዓ/ም ድረስ ሥራዎቻችሁን በዩኒቨርሲቲው ኢ-ሜይል አድራሻ፡-

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ከጋርዱላ ዞን ጋር በመተበበር የዲራሼ ብሔረሰብ ባህላዊ የትንፋሽ ሙዚቃ መሣሪያ(ፊላ) በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ በተዘጋጀ ረቂቅ ትልመ ሃሳብ(Draft Project Proposal) ዙሪያ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሚያዝያ 12/2016 ዓ/ም ውይይት ተካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የዲራሼ ብሔረሰብ ባህላዊ የትንፋሽ ሙዚቃ መሣሪያ(ፊላ)በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ውይይት ተካሄደ

- Details
Arba Minch University (AMU) Research Team wins $100,000 Funding of the Armauer Hansen Research Institute, AHRI, call for Grand Challenges Ethiopia (GCE). The Project is entitled “AI-Based Malaria Incidence Prediction under Current and Future Climate in Southern Ethiopia, AIM-Clim”. The AIM-Clim project brings together experts from diverse research fields including climate science, public health, artificial intelligence, and ecology.
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት የስርጭት መጠን፣ መንስዔዎችና የሚያስከትለው ጉዳት ላይ የሠራውን ጥናት ይፋ አደረገ
- የነፃ ሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ለሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተጠቂዎች ለማድረስ የሚያስችል የጋራ ትብብር ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ
- AMU-IUC Inaugurates the 1st Daycare Center at AMU and Trains Caregivers
- የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ ክንውን ሪፖርት ተገመገመ