
- Details
በወባ በሽታ መከላከልና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እየሠራ በሚገኘው “AMU-SENUPH II” ፕሮጀክት የወባ በሽታን ለመከላከል በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያና ምዕራብ ዓባያ ወረዳዎች በተመረጡ ቀበሌዎች ቤቶችን በማሻሻል እና የአይቨርሜክቲን (Ivermechtin) የከብት ህክምና (House Screening and Ivermechtin Cattle Treatment) በወባ ስርጭት ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመረዳት የመስክ ትግበራ ለመጀመር የሚያስችል ውይይት ከባለድርሻዎች ጋር ሚያዝያ 18/2015 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ በተለያዩ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋር ሚያዝያ 30/2015 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋር ውይይት አካሄደ

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮምፒውቲንግና ሶፍትዌር ምኅንድስና ፋከልቲ መምህር የተዘጋጀው የጋሞኛ ቋንቋ ኤሌክትሮኒክ መዝገበ ቃላት መተግበሪያ የዩኒቨርሲቲውና የዞን አመራሮች፣ መምህራን እና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት ሚያዝያ 12/2015 ዓ/ም ይፋ ተደርጓል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው የጋሞኛ ቋንቋ ኤሌክትሮኒክ መዝገበ ቃላት መተግበሪያ ይፋ ሆነ

- Details
"HUMAN BRiDGE" የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የሚሆኑ ዘመናዊና በሪሞት የሚሠሩ 240 የታካሚና የቀዶ ጥገና ክፍል አልጋዎች፣ ፍራሾች፣ ዊልቸሮች፣ ክራንቾች፣ የቀዶ ጥገና ክፍል መብራቶች እና ሌሎች የሕክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ሚያዝያ 22/2015 ዓ/ም ለሆስፒታሉ አስረክቧል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: "HUMAN BRiDGE" የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከሠላም ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ‹‹ሀገር በቀል ዕሴቶችን ለዘላቂ ሠላምና ጠንካራ ሀገራዊ መንግሥት ግንባታ›› በሚል ርዕስ ከሚያዝያ 20-21/2015 ዓ/ም ሀገራዊ አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ‹‹ሀገር በቀል እሴቶችን ለዘላቂ ሠላምና ጠንካራ ሀገራዊ መንግሥት ግንባታ›› በሚል ርዕስ አውደ ጥናት ተካሄደ
- AMU Launches Collaborative Grand Research Project on Irrigation & Renewable Energy Technologies worth £279,132 (18.9 Million ETB) at Garda Marta, Gamo Zone
- የዶሮ ሽያጭ ማስታቂያ
- AMU-IUC Transversal SP7 Coordinator's Appointment Vacancy Ad (Second Time)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጋርዳ ማርታ ወረዳ የ18.9 ሚሊየን ብር አዲስ የትብብር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ