የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ በአባያ ካምፓስ በሚገኘው ስቴዲየም የ2018 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንዲችል ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር በትብብር እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው ስፖርት አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ አሰግድ ከተማ በዩኒቨርሲቲው አባያ ካምፓስ የሚገኘው ስቴዲየም አስፈላጊ ግብአቶች ከተሟሉለት 20 ሺህ ሰዎችን የሚያስተናግድና የተለያዩ አገር አቀፍና አህጉር አቀፍ ወድድሮችን ማድረግ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህንን መሠረት በማድረግ ስቴዲየሙ የ2018 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንዲችል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አቶ አሰግድ ተናግረዋል፡፡ የመጫወቻ ሜዳው የአገሪቱ ሊግ በሚፈልገው ስታንዳርድ ልክ እንዲሆን ሥራው 90 ከመቶ መጠናቀቁን የገለጹት አቶ አሰግድ የመልበሻ፣ የሕክምናና የሚዲያ ክፍሎችን ጨምሮ ሌሎች ወሳኝ ተግባራትን በስታንዳርዱ መሠረት የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ከዋናው የመጫወቻ ሜዳ ባሻገር ለውውድሩ ለሚመጡ ቡድኖች የሚሆኑ የመለማመጃ ሜዳዎች በዋናው ግቢ እና ኩልፎ ካምፓስ እንዲሁም በከተማው በሚገኙ ት/ቤቶች እየተዘጋጁ መሆኑን አንስተዋል፡፡ እየተደረገ የሚገኘው ዝግጅት ከፕሪሚየር ሊግ ባሻገር እንደ ከፍተኛ ሊግ፣ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ያሉ ትልልቅ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ጭምር ሲሆን መሰል ውድድሮችን ማዘጋጀት መቻሉ የስፖርት ቱሪዝምን በማጎልበት ለከተማውም ሆነ ለዩኒቨርሲቲው ትልቅ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንም አቶ አሰግድ አንስተዋል፡፡

በቅርቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ሊግ ካምፓኒ ጋር በመሆን ምልከታ የሚያካሂዱ መሆኑንም አክለዋል፡፡


ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት