የዩኒቨርሲቲው አመራር አካላትና መምህራን በቀን 01/4/2015 ዓ/ም ሰፊ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ከሰኞ (ታኅሣሥ 03/2015 ዓ/ም) ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራውን በተሟላ ደረጃ ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በመሆኑም ሁሉም መምህራን እና ተማሪዎች በትምህርት ክፍለ ጊዜያችሁ መሠረት በመማር ማስተማር ሥራው ላይ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው ከአደራ ጭምር ይገልጻል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ