የ3 ዓመት የፋርማሲ ተማሪ የሆነችው ተማሪ ሜሮን ካፒታ ዋልጬ ባጋጠማት የኩላሊት ሕመም በሕክምና እየተረዳች ቢሆንም ጉዳዩ ከአቅም በላይ በመሆኑ ወደ ውጭ ሀገር (ሕንድ) ተልካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ  እንዲደረግላት በሐኪሞች ተወስኗል፡፡

የቤተሰቦቿ አቅም ለሕክምናው የተጠየቁትን ገንዘብ መጠን መሸፈን ሰለማይችል የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ካውንሰል አባላት "ለወገን ደራሽ ወገን ነው" በማለት ከዕለት ምግባቸው በመቀነስ ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የካውንስሉ አባላት ከመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ገንዘብ ለማሰባሰብ ከመስከረም 24/2017 ዓ/ም ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው ዋና ካምፓስን ጨምሮ በሁሉም ካምፓሶች ስለሚንቀሳቀሱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራን የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም ሌሎች የአካባቢው ማኅበረሰብ የአቅማችሁን ያህል ድጋፍ እንድታደርጉ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ካውንስል ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት ካውንስል

በባንክ መርዳት ለምትፈልጉ፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000021582046

ዳሽን ባንክ 5052031563011

ብርሃን ባንክ 1030252633077

አቢሲንያ ባንክ 203463642

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት