የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ ግምገማ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጳጉሜ 2/2016 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የ10 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድን መሠረት አድርጎ በስምንት ዋና ዋና ግቦች ተከፋፍሎ የሪፎርም ሥራዎችንና ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብሎ የያዛቸውን መሠረታዊ ጉዳዮች አካቶ የተዘጋጀውን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2017 ዕቅድ ለቦርዱ አቅርበዋል፡፡  እንደ ፕሬዝደንቱ በቦርዱ ውይይት በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፣ በቀደሙ ስብሰባዎች የተወሰኑ ውሳኔዎች አፈጻጸም፣ ከመዋቅር አደረጃጀት አንጻር ያሉ አጀንዳዎች እንዲሁም በፌዴራል ኦዲት ግኝት መሠረት የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች ተካተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ መጀመሪያ ላይ የቦርድ አባላቱ ከዩኒቨርሲቲው አመራርና ሠራተኞች ጋር በመሆን በድኅረ ምረቃ ሕንጻ አካባቢ ባለው ቦታ ለምግብነትና ለውበት የሚያገለግሉ ችግኖች ተከላ አከናውነዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት