አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥን ቡድን ለዩኒቨርሲቲው በሰጠው ግብረ መልስና ሌሎች ተያያዥ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋር ከታኅሣሥ 04-11/2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም ካምፓሶች ከአስተዳደር ሠራተኞችና መምህራን ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ውይይቱ በመልካም አስተዳደር ተግዳሮቶች፣ በትምህርት ጥራት፣ የተማሪዎች መኝታ፣ መመገቢያ፣ መማሪያና ማንበቢያ ቦታዎችን ምቹና ማራኪ በማድረግ፣ ጤናማ ተቋማዊ ግንኙነት በመፍጠር፣ ውጤታማ የመዋቅር ማሻሻያ በማድረግ፣ የዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝ አስተዳደር ለመሸጋገር እያደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት፣ የምርምር ፕሮጀክቶችን መጠንና  የገቢ ማስገኛ አማራጮችን በማሳደግና ሌሎች ተያያዥ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ውይይቱ ከዋናው ግቢ የአስተዳደር ሠራተኞችና መምህራን ጋር ታኅሣሥ 04/2016 ዓ/ም የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም በዓባያ፣ ነጭ ሣርና ኩልፎ ካምፓሶች ታኅሣሥ 8/2016 ዓ/ም፣ በጫሞ ካምፓስ ታኅሣሥ 9/2016 ዓ/ም እንዲሁም ሳውላ ካምፓስ ታኅሣሥ 11/2016 ዓ/ም እንዲካሄድ ታቅዷል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት