የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 12ኛ ክፍል ተማሪ የአብሥራ ፍፁምና ዳግም ሰለሞን የጋሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከሰኔ 10 – 15/2016 ዓ/ም ባዘጋጀው ዞናዊ የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ላይ የፈጠራ ሥራዎችን በማቅረብ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና ኮሚዩኒቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዕውቅናና የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
ተማሪዎቹ በሥራ ሰዓት የመምህራንን ሰዓት/ክፍለ ጊዜ መቆጣጠር የሚያስችል ሶፍትዌር ያበለጸጉ ሲሆን በዞን ደረጃ የተለያዩ ተወዳዳሪዎች በተገኙበት ባቀረቡት የፈጠራ ሥራ በክልል ደረጃ ሥራቸውን እንዲያቀርቡ ከተመረጡ ፈጣሪዎች መካከል መሆን ችለዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት