የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ታዳጊ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከሐምሌ 10/2016 ጀምሮ በሀዋሳ ሲካሄድ በቆየው የ3ኛው ታዳጊ ሴቶች እግር ኳስ ምዘና ውድድር አሸናፊ ሆኗል፡፡ ቡድኑ ዛሬ አርባ ምንጭ ሲደርስ በዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ማኅበረሰብ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ አርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው በእግር ኳስ ዘርፍ ከፍተኛ አቅም ያለው መሆኑን ተናግረው የዩኒቨርሲቲው ቡድን ያስመዘገበው ውጤት በአርባ ምንጭ ከተማ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በተጣለበት ማግስት መሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ለመስኩ ዕድገትና ውጤታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም ፕሬዝደንቱ ጠቁመዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ አሰግድ ከተማ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት በዘርፉ ፍላጎትና ችሎታ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶችን በፕሮጀክት አደራጅቶ እያሠለጠነ መቆየቱን አስታውሰው ዩኒቨርሲቲው በሁለቱም ፆታዎች ከዚህ ቀደም በተካሄዱ መሰል ወድድሮች ውጤታማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በፕሮጀክቱ ሲሳተፉ ከነበሩ ታዳጊዎች መካከል እስከ አሁን 16 ወጣቶች በሀገሪቱ የተለያዩ ክለቦች ተመርጠው እየተጫወቱ እንደሚገኙ አቶ አሰግድ ገልጸዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት