የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከጤና ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዩኒቨርሲቲው ማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ የካቲት 2/2017 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታ ጋልቻ ሆስፒታሉን በተሟላ አቅም ወደ ሥራ ለማስገባት ጥሩ ሂደት መኖሩን ጠቅሰው በተለያዩ ጉዳዮች ሃሳብ ለመለዋወጥና የሚጎድሉ ግብዓቶችን ለሟሟላት ውይይቱ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ መድረኩ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ጥሩ ግንዛቤ የተፈጠረበት እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ደስታ ለቀጣይ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚረዳ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጤና ትምህርት እና ሕክምና አገልግሎት ኮርፖሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ብርሃኑ አንዳርጌ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በኩል በሚመጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አማካኝነት የሚደረጉ ተደጋጋሚ ጉብኝቶችና ውይይቶች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረት ያመላክታል ብለዋል፡፡ ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንዲገባ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ከማሟላትና ለባለሙያዎች ቴክኒካዊ ድጋፎችን ከማድረግ አንጻር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል፡፡
በጤና ሚኒስቴር የሜዲካል ሰርቪስ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢሊባቡር ባኖ ሆስፒታሉን ወደ ሥራ ለማስገባት ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው ግዙፍ በመሆኑ ልዩ ትኩረት የሚሻ መሆኑንና የአንድ አካል ብቻ ሳይሆን የበርካታ አካላት ተሳትፎና ርብርብ የሚያስፈልገው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር በኩልም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው ከክልል እስከ ወረዳው ያሉ አካላትም የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለሆስፒታሉ በሙሉ አቅም ሥራ መጀመር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ዶ/ር ኢልባቡር አረጋግጠዋል፡፡
በዕለቱ ኃላፊዎቹ በሆስፒታሉ የሚገኙ የተለያዩ የሕክምና ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት