አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት የሚደረግበት ቀን ኅዳር 12/2014 ዓ.ም
ምዝገባ የሚካሄድበት ቀን ኅዳር 13 እና 14/2014 ዓ.ም
መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበት ኅዳር 15/2014 ዓ.ም በመሆኑ፡-
· አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ
· አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስና የስፖርት ትጥቅ
· ስምንት 3 x 4 የሆነ ጉርድ ፎቶ እና
· ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) ይዛችሁ
እንድትመጡ እያሳወቅን ከተጠቀሰው ቀናት ውጭ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እንገልጻለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት